image
image
image
image
image

ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች መጠቀምን የሚከለክል አዋጅ ተግባራዊ መሆኑ ተገለፀ፡:

ጥር 27, 2018
በአሁኑ ወቅት የከተሞች መስፋፋት፣ የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የኢኮኖሚ እድገት ሂደትና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ምክንያት በህዝቡ ዘንድ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚዉሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች ጥቅም ላይ ከዋለ በኋለ በቀጥታ ወደ አካባቢ የሚወገዱ በመሆኑ፤ ይህም የፕላስቲክ ውጤቶች በአፈር ውስጥ ሳይበሰብስ ከአንድ መቶ ዓመት በላይ የሚቆይ በመሆኑ የውሃ አካላት መበከል፤ ብዝሃ ህይወት መጎዳት፣ በምርትና ምርታማነት ላይ ተፅዕኖ ከማድረስ በላይ የሰውንና አካባቢ ጤናን በማወከል ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ዜጎች በንጽሕ እና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብትን ለማረጋገጥ፤ የዜጎችን ጤንነት ከከንሰርና ከሌሎችን በሽታዎች በመከላከል፣ ዘላቂ የአካባቢ አያያዝ ስርዓትን ለማስፈን መንግስት ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ማምረት፣ ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከማቸት፣ መሸጥ እና መጠቀም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ 1383/2017 የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ዜጋ ህጉን በማክበር ራሱን እና አካባቢውን ከፕላስቲክ ብክለት በመከላከል እንዲሁም ከህግ ተጠያቂነት እራሱን በመጠበቅ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ይህን አዋጅ አፈፃፀም ለማስጠበቅ በክፍለ ከተማው ባሉ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከጥር 23 2018ዓ.ም ጀምሮ የቁጥጥር እና ክትትል ስራ መጀመሩን አስታውቋል:: የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች