image
image
image
image
image

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስርዓትን ለመገንባት የአካባቢ ብክለትን መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

መስከረም 4, 2018
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀሙን እና የ2018 በጀት አመት እቅዱን ከሲቪክ ማህበራት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡ ጽ/ቤቱ በተጠናቀቀው በጀት የአየር ፣ የውሃ ፣ የአፈርና የድምጽ ብክለቶች ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት በወንዝ ዳርቻ ልማቶች ላይ ብክለት መከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ ወንዞችን መከላከል መቻሉ የአካባቢ ጥበቃና የልማት ስራዎች ማከናወኑን በሪፖርቱ ላይ ተብራርቷል ። የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሃና ምህረቱ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው በጀት አመት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የአካባቢ ግንዛቤ የማጎልበትና ከመቆጣጠር አንፃር ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ በርካታ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን በመግለጽ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማት የመገንባት ስራውም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ እየተተገበረ ላለው የአረንጓዴ ልማት መርሃ-ግብርም የችግኝ በማፍላትና የመትከያ ጉድጓድ በማዘጋጀት፣በመትከልና የጽድቀት መጠን ለማሳደግ በመንከባከብና በመጠበቅ ውጤታማ ስራ ማከናወን መቻሉን ተገልጻል፡፡ በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የአከባቢ ብክለትን በመከላከል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን እና የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራሞችን አጠናክሮ በመስራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ በተያያዘም የመልካም አስተዳደር ስራዎችና ቅንጅተዊ አሰራሮች ዙሪያ ውይይት አካሄዷል። ጽ/ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላበረከቱ ባለ ድርሻ አካላት ፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች